How to Play

ምን ልበል? ጨዋታ አጨዋወት

ምን ልበል? የቤተሰብ እና ጓደኞች የካርታ ጨዋታ ነው። ግቡ የቡድን ጓደኞችዎ እርስዎ የሚገልጹትን ቃል እንዲገምቱት ማድረግ ነው፤ ነገር ግን መናገር የማትችሉት የቃላት ዝርዝር አለ። ቡድኖችን በእኩል መጠን ለሁለት ይከፈላሉ፣ ካርታዎቹ ይዘጋጃሉ፣ ከዚያም ተረኛ ቡድን ይመረጣል። ተረኛ ካልሆነው ቡድን አንድ ሰው ሰዓት ቆጣሪ ይሆናል፤ ለ1 ወይም 2 ደቂቃ ሰዓት ይያዛል። ከተረኛው ቡድን አንድ ሰው ፍንጭ ሰጪ ይሆናል፤ ለቡድኑ የማይባሉትን ቃላት ሳይጠቀሙ ዋናውን ቃል ያስገምታሉ። ማስረዳት የማይችሉት ቃል ካለ ማለፍ ይችላሉ፤ ነጥብ ግን አያስገኝም። በትክክል የሚያገኙት እያንዳንዱ ካርድ ለቡድንዎ ነጥብ ነው፣ ቡድኑ የዘለሏቸውወይም የተከለከሉ ቃላት የተናገሩባቸው ካርዶች ለሌላው ቡድን ነጥብ ናቸው።

ጨዋታው ሲጀመር

  1. ለሁለት እኩል ቦታ በመከፋፈል ሁለት ቡድኖች ይፍጠሩ
    • ወንዶች እና ሴቶችን ማጋጠም፣
    • ወላጆችን ከልጆች ጋር ማፎካከር፣
    • ወይንም ባልና ሚስትን የተለያየ ቡድን በማድረግ ሊጫወቱ ይችላሉ።
    • እያንዳንዱ ተራ ሲጀመር ለቡድኑ የሚያስረዳው ሰው በእጅ በቂ ካርታዎችን መያዝ እንመክራለን። 
    • ከፊት ያለውን ካርታ በሚያስረዱበት ጊዜ ሌሎች የቡድንዎ አባላት የያዙትን ካርታ ማሳየት አይችሉም። በስህተት ካዩት ካርታው ከጨዋታው ውጪ ይደረጋል፤ ነገር ግን ተቃራኒው ቡድን ነጥቡን አያገኝም።
    • የ1 ደቂቃ ሰዓት ይያዛል። ከተቃራኒው ቡድን አንድ ሰው ሞባይል ስልክ በመጠቀም ሰዓት የመያዝ ኃላፊነት ይሰጣቸዋል። እያንዳንዱ ተራ አንድ ደቂቃ ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ የምትችሉትን ያህል ቃላት በማስገመት ነጥብ ያገኛሉ።

የዙር አጨዋወት

Person explaining the guess word

  1. አስረጂው ሰው ለሌሎቹ የቡድኑ አባላት ካርታው ላይ ያሉትን ቃላት ሳይጠቀሙ ፍንጮች ይስጡ። ቃሉ በትክክል ከተገመተ ነጥብ ያገኛሉ። የተጻፉትን ቃላት በምንም አይነት ሁኔታ መጠቀም አይችሉም።
    • የማያውቁት ቃል ከደረሳችሁ ካርዱን መዝለል ይችላሉ። ነገር ግን፣ ካርድ ከዘለሉ ነጥብ ወደ ሌላኛው ቡድን ይሄዳል።
    • ገማቾቹ ትክክለኛውን ቃል መገመት አለባቸው፣ ስለዚህ ከተጠጉ፣ ወይም የቃሉን ክፍል ካገኙ፣ በትክክል እስኪያገኙትት ድረስ ፍንጭ መስጠት አለባችሁ።
    • የማይባሉትን ቃላት ከመናገር ይቆጠቡ። እያንዳንዱ ካርታ በጣም ግልጽ የሆኑ ከግምት ቃሉ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ቃላትን ይይዛል።
    • የተቃራኒው ቡድን አባላት ሰዓት ያያሉ፤ በተጨማሪም የማይባሉት ቃላት አለመባላቸውን ይከታተላሉ።
    • ሁለቱም ቡድን የራሱን በትክክል የተገመቱት ካርታዎች ይይዛል።

ነጥብ አያያዝ

ተረኛው ቡድን በትክክል ለተገመቱት ካርዶች ሁሉ አንድ ነጥብ ያገኛል። 

  • ለተወሰነ ነጥብ ወይም ለተወሰኑ ዙሮች ለመጫወት መወሰን ይቻላል። ለትልቅ ቡድኖች ሁሉም የቡድን አባል ፍንጭ ሰጪ ሆኖ አንድ ዙር እስከተጫወተ ድረስ መጫወት እንመክራለን።
  • ለአንድ ደቂቃ የተያዘው ሰዓት ያለቀበት ካርታ መቆጠር የለበትም።

ጨዋታው ሲያልቅ ሁለቱ ቡድኖች ያላቸውን ካርታዎች ይቆጥራሉ፤ የበለጠ የካርታ ቁጥር ያለው ቡድን ያሸንፋል!